በሶስት ቦታ ተከፋፍለው የነበሩትን የኢትዮጵያን ኮሙኒቲ አንድ ለማድረግና ለማዋሃድ ረጅም ጊዜ በወሰደው የማስማማት ጥረት እ.አ.አ.ጃኑዋሪ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የውህደትና የአንድነት ስምምነት ውል በአዲስ አበባ ሬስቱራንት ከፍተኛ ሕዝብ በተገኘበት መፈራረማቸው ይታወሳል።

በስምምነቱ መሰረት በአንድ ስም አዲስ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ እንዲቋቋም በተወሰነው መሠረት፦” በኮሎራዶ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ (COLORADO ETHIOPIAN COMMUNITY( C.E.C)” ተብሎ ስሙን በመሰየም እ.አ.አ ኦክቶበር 16 ቀን 2016 ዓ.ም በአውሮራ ቤተመጻሕፍት የስብሰባ አዳራሽ ከፍተኛ ሕዝብ በተሰበሰቡበት 9 (ዘጠኝ) አባላት ያሉት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በመምረጥ አዲስ ኮሙኒቲ ተቋቁሟል።

እንዲሁም ቀደም ብሎ ወደ ነበርንበት ችግር እንዳንመለስ የኮሙኒቲ ድርጅቱን በበላይ ሆኖ የሚመክርና የሚጠብቅ በአዲስ መዋቅር ከየእምነት ተቋማትና ከሕብረተሰቡ በተወከሉ 9(ዘጠኝ) አባላት ያሉት “የሕዝብ ባለአደራ ቦርድ” (BOARD OF PUBLIC TRUSTEE (B.O.P.T) እ.አ.አ. ኦገስት(ነሐሴ) 21 ቀን 2016 ከላይ በተጠቀሰው ስብሰባ አዳራሽ በተሰበሰበው ጠቅላላ ጉባኤ አዎንታ (confirmation) አግኝተው ሥራቸውን ጀምረዋል።

ይህ ውጤት የተገኘው ከብዙ ውጣ ውረድና አስቸጋሪ የማስማማት ጥረት በኃላ በመሆኑ ሕብረተ ሰቡም ሆነ በዚህ የተካፈልነው ሁሉ ደስተኞች ሆነናል። ለዚህ መልካም ውጤት የተደረሰው የእምነት ተቋማት አባቶች፣ አመራሮችና ምእመናን ለኮሙኒቲው አንድነት በአደረጋችሁት ከፍተኛ ትብብርና ድጋፍ ጭምር በመሆኑ በቸሩ ፈጣሪያችን ስም ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን ።

የሕብረተ ሰባችንን ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት የእምነት ተቋማትና የኮሙኒቲ ማህበረሰብ መደጋገፍ ጉልህ ሚና አላቸው ። በመሆኑም ይህንን በብዙ ጥረት የተገኘውን የኮሙኒቲ አንድነት ዘላቂነት እንዲኖረው ሕብረተ ሰቡ በአባልነት በመመዝገብ በፋይናንስና በሁለንተናዊ መልኩ ማጠናከርና መደገፍ ያስፈልጋል።ኮሙኒቲው የህብረተሰቡ ድርጅት በመሆኑ ምዕመኑም ይህንኑ ተገንዝበው በኣባልነት እንዲመዘገቡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ኢትዮጵያ በአንድነትዋ ለዘላለም ትኑር!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.