ጠንካራ ኮሙኒቲ ለመመ ሥረት ከአመት በላይ በፈጅ ጊዜ ሰፊ ዝግጅት ተደርግዋል።
========================================
1) ይህንን እውን ለማድረግ ምን ተሰርቶ ነበር ?
===================
።።።።።።ተከፋፍለው የነበሩት 3ቱ ኮሙኒቲዎች በመስማማት የውህደት ስምምነትውል መፈራረማቸው፤
።።።።።።መሰረታዊ (core value ) የተባሉት የሶስቱም ኮሙኒቲ ጥያቄዎች በኮሙኒቲው መተዳደሪያ ሕገ ደንብ ውስጥ መካተታቸው፤
።።።።።።ሕገደንቡ በተወሰነ ደረ ጃ መሻሻሉ፤
።።።።።።ከሁሉም በላይ እንደከዚህ በፊት እንዳይከፋፈሉ የኮሙኒቲውን ህልውና በበላይ ሆኖ የሚጠብቅ የህዝብ ባለአደራ መቕዋቕዋሙ፤
።።።።።።ኮሙኒቲው ከዘር፣ ከሃይማኖት፣ ከፓለቲካ ገለልተኛ ሆኖ ሁሉንም ኢትዮ ጵያዊ እኩል የማገልገል ዓላማ ላይ መመስረቱ፣እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም፣ በቅርቡ የሚመሰረተውን አዲሱን ኮሙኒቲ ከዚህ በፊት ከነበሩት ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል ተብሎ ይታመናል።
2) ህብረተሰቡ ከኮሙኒቲ ድርጅቱ ምን ዓይነት አገልግሎት ይጠብቃል?
====================
።።።።።።መጠጊያ አጥተው በየመንገዱ የሚንከራተቱ፤
ሥራ አጥተውየተቸገሩ፤ታመው አቅም በማጣት ሕክምና የማያገኙ፤አጉል ልማድ ውስጥ ገብተው መውጫ ያጡ ወገኖቸችንን ጠንካራ ኮሙኒቲ ተቕዋቁሞ እንዲረዳ ሕብረተሰቡ ይፈልጋል።
።።።።።።በሞት አደጋ ጊዜ አስከሬን ለመቅበር የሚያስችል
የገንዘብ አቅም እንዲኖር ሕብረተ ሰቡን በማስተባበርና በማደራጀት የቀብር ሥርአት ፈጻሚ ማህበር(እድር) በማቕዋቕም አስከሬን በወቅቱ እንዲቀበር ወይም ወደ ሀገር ቤት እንዲላክ ሊያደርግ የሚችል ጠንካራ ኮሙኒቲ ህብረተሰቡ ይፈልጋል። ለሳምንታት አስከሬን አስቀምጦ ፣ደብተር ዘርግቶ ፣ በየቦታው መለመኑ አሳፋሪ መሆኑን ህብርተሰቡ ይገነዘባል።
።።።።።።ለችግሩም ሆነ ለደስታ የሚገለገልበትንና የሚሰበሰብበትን፤በአዘቦትም ሆነ ለመዝናኛ የሚገናኝበትን የኮሙኒቲ ማዕከል እንዲኖረው ይፈልጋል።
3) የኮሙኒቲ ድርጅቱ ከህብረተ ሰቡ ምን ይጠብቃል?
===================
።።።።።።ኮሙኒቲው ከህብረተሰቡ ሙሉ ድጋፍን ይፈልጋል።የህብረተሰቡ ድጋፍ የሌለው የኮሙኒቲ ድርጅት ምንም መሥራት ስለማይችል፦
።።።።።።ህብረተሰቡ ድርጅቱ የራሱ መሆኑ አውቆ ጠንካራ የኮሙኒቲ አመራሮችን በነቂስ ወጥቶ መምረጥ ይጠበቅበታል።
።።።።።።የኮሙኒቲ ድርጅቱ ያለህዝብ ድጋፍ ብቻውን ምንም መስራት እንደማይችል ታውቆ ህብረተሰቡ በአባልነት ተመዝግቦ ወርሃዊ መዋጮ በማድረግ መብትና ግዴታውን መወጣት ይጠበቅበታል።
።።።።።።ጠንካራ ራዕይ (vision ) ያላቸውን በመምረጥ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለልጆቻችንም መልካም አርአያነትን፤አንድነትንና ፍቅርን ለማውረስ የህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎ የግድ ይላል።
4) ከእጩ ተመራጮችና ጠቅዋሚዎች ምን ይጠበቃል?
=================
።።።።።።ህብረተሰቡን የማገልገል የውዴታ ግዴታ ኃላፊነት መወጣትን፤መገልገል ብቻ ሳይሆን ማገልገልን፤ቅን ልቦናንና ፈቃደኝነትን፤በዘር፡በሃይማኖት ፡በፖለቲካ ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ በእኩልነት ማገልገልን፤ ለልጆቻችን መከፋፈልን ሳይሆን አንድነትንና ፍቅርን የማውረስ ባህል ራእይ ያለው መሆንን፤ ለመመረጥ ተለምኖ ሳይሆን በፈቃደኝነትና ምረጡኝ ብለው በመወዳደር ሁሉም በየተራው ህብረተሰቡን የማገልግል ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅብናል።
ሰለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን በየበኩላችን ከተወጣን ጠንካራ ኮሙኒቲ ሆነን ተገቢውን አገልግሎት ማግኘትና መስጠት እንችላለን ።
አንድነታችን ይጠንክር! !!
ጠንካራ ኮሙኒቲ ሊኖረን የሚችለው አንድነት ሲኖረን ነው!!!
ኢትዮጵያ በክብር አንድነትዋ ተብቆ ለዘላለም ትኑር።
የጊዜያዊ አስተባባሪ ግብረሃይልና የሕዝብ ባለአደራ ቦርድ
,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.