በእድር እንደራጅ!!!
በሰላም ሀገር እንደልባችን ሰርተን ገንዘብ እያገኘን፤ ባለመደራጀታችን ብቻ ሳናጣ ያጣን ይመስል በሞት ጊዜ፤ አስከሬን ለሳምንታት አስተኝተን ፤ ደብተር ዘርግተን፤ በየእምነት ተቋማትና ንግድ ሱቆች ዞረን በሰቀቀን ለምነን በምናገኘው የቀብር ማስፈፀሚያ ገንዘብ ወደ መቃብር መውረድን የመሰለ አሳፋሪ ነገር የለም። 

በመሆኑም ይህንን አሳፋሪ የልመናን ባህል ለማስቀረት በማህበር አደራጁን ጥያቄ ከህብረተስቡ ሲቀርብ ቆይቷል።

ይህንኑ የህብረተሰቡን ጥያቄ መሰረት በማድረግ በኮሎራዶ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ በእቅድ ይዞ፤ሰፊ ጥናት አድርጎ ፤በዘር ፤በሃይማኖት ፤በፖለቲካ፤ሳንለያይ ኢትዮጵያውነትን ብቻ መሰረት ያደረገ ፤ሁሉን አቀፍ መረዳጃ ማህበር እድር በመመሥረት ላይ ይገኛል።

ሰለዚህ ከአሁን ጀምሮ እስከ ጁላይ 30 በየእምነት ተቋማትና የስራ አካባቢዎች በምናደርገው የአባላት ምዝገባ ቅጹን በመውሰድና በመሙላት ወይም ከዚህ ቀጥሎ በተዘጋጀው ፎርም on line በመመዝገብ እንድታመለክቱ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ፤እድሩን ለማቅዋቋም የሰው ብዛት ማወቅ ወሳኝ በመሆኑ ፤በአሁኑ ጊዜ ምዝገባ ብቻ እንጂ ገንዘብ አንቀበልም።

ገንዘብ መቀበል የምንጀምረው የተመዘገበው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ የእድሩን ደንብና መመሪያ አጽድቆ፤የእድሩን አመራር አካላት ከመረጠ በኋላ ይሆናል።

ሰለዚህ ዛሬ በህይወት እያለን የእድሩ አባል በመሆን እጅግ አነስተኛ ገንዘብ ወርሃዊ መዋጮ በመክፈል ልመናን በማስቀረት ፤ራሳችን፤ቤተሰባችንና ፤ወገናችን ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ በክብር ለመሸኘት ወይም በክብር ወደ ሀገር ቤት ለመላክ ፈጥኖ ደራሽና አስተማማኝ አለኝታ በሚሆነን በእድር መረዳጃ ማህበር እንደራጅ !!!
ልመና አሳፋሪ ነውና ይቁም ! !!
ህብረታችንና አንድነታችን ሃይላችን ነው ! !!
ኢትዮጵያ በአንድነትዋና በነፃነትዋ ለዘላለም ትኑር !!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.