በቀብር ጊዜ ልመናን ለማስቀረት በእድር እንደራጅ!!!

በእድር እንደራጅ!!! በሰላም ሀገር እንደልባችን ሰርተን ገንዘብ እያገኘን፤ ባለመደራጀታችን ብቻ ሳናጣ ያጣን ይመስል በሞት ጊዜ፤ አስከሬን ለሳምንታት አስተኝተን ፤ ደብተር ዘርግተን፤ በየእምነት ተቋማትና ንግድ ሱቆች ዞረን በሰቀቀን ለምነን በምናገኘው የቀብር ማስፈፀሚያ ገንዘብ ወደ መቃብር መውረድን የመሰለ አሳፋሪ ነገር የለም።  በመሆኑም ይህንን አሳፋሪ የልመናን ባህል ለማስቀረት በማህበር አደራጁን ጥያቄ ከህብረተስቡ ሲቀርብ ቆይቷል። ይህንኑ የህብረተሰቡን ጥያቄ መሰረት … More በቀብር ጊዜ ልመናን ለማስቀረት በእድር እንደራጅ!!!

ምስጋና

በሶስት ቦታ ተከፋፍለው የነበሩትን የኢትዮጵያን ኮሙኒቲ አንድ ለማድረግና ለማዋሃድ ረጅም ጊዜ በወሰደው የማስማማት ጥረት እ.አ.አ.ጃኑዋሪ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የውህደትና የአንድነት ስምምነት ውል በአዲስ አበባ ሬስቱራንት ከፍተኛ ሕዝብ በተገኘበት መፈራረማቸው ይታወሳል። በስምምነቱ መሰረት በአንድ ስም አዲስ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ እንዲቋቋም በተወሰነው መሠረት፦” በኮሎራዶ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ (COLORADO ETHIOPIAN COMMUNITY( C.E.C)” ተብሎ ስሙን በመሰየም እ.አ.አ ኦክቶበር 16 ቀን … More ምስጋና